Assosa University

የማህበራዊ ሳይንስ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ተጀመረ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ዛሬ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተጀምሯል።

በዩኒቨርሲቲው ፈተናቸውን እንዲወስዱ የተመደቡ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት የእንግሊዝኛ ትምህርት ፈተናቸውን በሰላም እየወሰዱ ነው።

የፈተናውን ሂደት የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና የፈተናው አስተባባሪዎች በየፈተና ክፍሎች በመዘዋወር የተከታተሉ ሲሆን፣ ፈተናው ያለምንም ችግር እና በተረጋጋ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ዙር በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ከአጎራባች የምዕራብ ወለጋ አካባቢ ትምህርት ቤቶች የተመደቡ ከ1,500 በላይ ተማሪዎች በወረቀትና በኦንላይን የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና እየወሰዱ ይገኛሉ።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የፈተናው ሂደት በሰላም እንዲካሄድ አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶች አስቀድሞ በማጠናቀቅ ተማሪዎች ፈተናቸውን በተረጋጋ መንፈስ እንዲወስዱ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተገልጧል፡፡

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

Website: www.asu.edu.et

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *