Assosa University

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአራተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ገለጻ ተደረገ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ የአራተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ስለ ፈተናው አሰጣጥ፣ የፈተና ሂደት እና የፈተና ሥነ-ምግባር ገለጻ ተደርጓል።

ገለጻውን የሰጡት በትምህርት ሚኒስቴር የፈተና አስተባባሪ አቶ ቶማስ ገቢባ ሲሆኑ፣ ስለ ፈተናው አሰጣጥ ሂደት፣ የፈተና ሥነ-ምግባር፣ የሚፈቀዱ እና የማይፈቀዱ ተግባራት፣ እንዲሁም ተፈታኞች ሊከተሏቸው ስለሚገቡ አጠቃላይ ደንቦች ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መ/ር ደሳለኝ አየለ፣ ተፈታኞች በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ ወቅት ሊያውቋቸው ስለሚገቡ አገልግሎቶች፣ በግቢው ውስጥ የተፈቀዱ እና የተከለከሉ ተግባራት፣ እንዲሁም ሊያከብሯቸው ስለሚገቡ የዩኒቨርሲቲው ህግና ደንቦች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል።

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ ዶ/ር ወንድም መኩሪያ በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው ፈተናው በሰላም፣ በሥርዓት እና ያለምንም ችግር እንዲካሄድ የሚያስፈልጉ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅቶች አስቀድሞ ማጠናቀቁን ገልጸው፣ ተፈታኞችም በመረጋጋት እና የፈተናውን ደንብ በማክበር ፈተናቸውን እንዲወስዱ አሳስበዋል።

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲው የሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ሀብታሙ ሸንቁጥ፣ በአራተኛው ዙር የፈተና መርሃ ግብር ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ከምዕራብ ወለጋ አካባቢ የተውጣጡ ከ1,500 በላይ ተፈታኞች በወረቀት እና በበይነ መረብ (Online) የፈተና ስርዓት እንደሚፈተኑ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኞች ምቹ የፈተና አካባቢ በመፍጠር አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን በመግለጽ፣ ለሁሉም ተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ እና የተሳካ ውጤት እንዲገጥማቸው ዶ/ር ሀብታሙ ተመኝተዋል

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

Website: www.asu.edu.et

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *