Assosa University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር ክልላዊ የቴክኖሎጂና ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ውድድር እያካሄደ ነዉ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር የ2018 በጀት ዓመት የ5ዉኛ ዙር ክልላዊ የቴክኖሎጂና ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ውድድር እያካሄዱ ይገኛል፡፡

በውድድሩ መርሃ ግብር ላይ የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኋላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ክህሎት ለሁሉም የልማት ተግባራት መሠረት መሆኑን ገልፀው ቢሮዉ ከዩኒቨርሲቲዉ ጋር በመተባበር የክልሉን ማሕበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ቴክኖሎጂ ለሀገርና ለክልል ልማት ያለውን የማይተካ ሚና በመጠቆም፣ ይህ ውድድር የክህሎት ባህልን ለማዳበር እና ተግባራዊ ምርምሮችን ለማጠናከር አስፈላጊ መድረክ መሆኑን አቶ አብዱሰላም ገልጸዋል፡፡

በዉድድር መርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲተዉ የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዑመር ሸሪፍን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት የተጀመረ ሲሆን ስለ ውድድሩ ዓላማና አቀራረብ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ልማትና ሽግግር ዙሪያ በአቶ ከተማ በቀለ እና በመ/ር ፍቃዱ እሸቱ ገለፃ ተደርጓል፡፡

ውድድሩ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ዳኝነት እየተመራ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን፣ በውድድሩ 3 የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችና 4 ተግባራዊ የምርምር ፕሮጀክቶች በ19 አሰልጣኞች የተሰሩ ስራዎች እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከክልሉ ተቋማት ጋር በመተባበር ቴክኖሎጂ ተኮር ሥራዎችን እና ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ የክልሉ ማህበረሰብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ለሀገር እድገት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሚገኝ ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከተሉን

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

Website: www.asu.edu.et

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *