


በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit Exam) ዛሬ መሰጠት ተጀምሯል።
ከሰኔ 04 እስከ ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው ይህ ፈተና በዩኒቨርሲቲው በተዘጋጀው የፈተና መርሃ ግብር መሠረት ያለምንም ችግር እየተካሄደ መሆኑን የፈተና ማዕከል ኃላፊው አቶ ጌትነት ታመነ ገልጸዋል።
አቶ ጌትነት እንደተናገሩት፣ ፈተናው በተገቢው የፈተና ሥነ-ሥርዓት መሠረት በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ ለፈተናው ስኬታማ አፈጻጸም የሚያስፈልጉ ሁሉም ዝግጅቶች አስቀድመው መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።
በዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ ከ3,200 በላይ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተናን እንደሚወስዱ የተገለጸ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው ፈተናው በሰላም፣ በፍትሃዊነት እና በጥራት እንዲካሄድ የተለያዩ የቁጥጥርና የድጋፍ ሥርዓቶችን በመዘርጋት እየሰራ መሆኑንም ተጠቁሟል።