Assosa University

ዩኒቨርሲቲዉ ከግልገል በለስ ትምህርት ኮሌጅ ጥምረት በሚተገበሩ ፕሮግራሞች ዙሪያ አብሮ ለመሥራት ከGeneva Global ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከግልገል በለስ ትምህርት ኮሌጅ ጥምረት በሚተገበሩ ፕሮግራሞች ዙሪያ አብሮ ለመሥራት ከGeneva Global ጋር የመግባቢያ ስምምነት ፈጽሟል።

Geneva Global በኢትዮጵያ የመምህራን ትምህርት ሥርዓትን ማጠናከር እና የመማር-ማስተማር ሂደቱን ጥራት የሚያሻሽሉ ዘላቂ ተሃድሶዎችን ተቋማዊ ማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ የሚገኝ ጠቋም እንደሆነ በመድረኩ ተገለጿል። አሁን ላይ ከ15 ዩኒቨርሲቲዎች እና 14 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ጋር አብሮ ለመሥራት አጋርነት መፍጠሩ የተገለፀ ሲሆን ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲና ከግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር በቀጣይ አምስት ዓመታት አብሮ በሚከናወኑ ሥራዎች ዙሪያ በፊርማዉ ሥነ ሥርዓት ላይ በዝርዝር ቀርቦ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በመግባቢያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት እንዲሻሻል ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር አብሮ እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ ይህ አኩሪ ሥራ ለበለጠ እንዲጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲዉ ከግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በተጨማሪ በክልሉ ከሚገኙ የግብርናና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ፕሬዝዳንቱ በመድረኩ ገልፀዋል።

በስምምነቱ አዲስ የCTE አሰልጣኞችን ማዘጋጀት (Preparing new CTE instructors)፣ በማስተማር ሥራ ላይ ያሉ የኮሌጅ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ መምህራንን ክህሎት ማሳደግ (Enhancing skills of current teachers)፣ የትምህርት አመራርነትን ማጠናከር (Strengthening instructional leadership)፣ የተማሪዎችን የሽግግር ሂደት መደገፍ (Supporting students transition)፣ ሁሉን አቀፍነትን እና የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትን ማሻሻል (Advancing inclusion and gender equity)፣ መምህራንን ማበረታታት/ማነቃቃት (Motivating educators)፣ ቀጣይነት ያለው የትምህርት ሥርዓት መገንባት (Building a sustainable educational system) የተካተቱ ናቸዉ::

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *