የኢምፓክት የጤናና ስነ-ህዝብ ክትትል ስርዓት (Impact HDSS) የድጋፍና ክትትል ቡድን ሐምሌ 2/ 2018 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሐምሌ ጉብኝት በማድረግ፣ በባንባሲ የጤናና ስነ-ህዝብ ክትትል ስርዓት (HDSS) ላይ እየተከናወኑ ያሉ የፕሮጀክቱ ተግባራትን እና የስራ አፈጻጸምን በዝርዝር ገምግሟል።
በዚሁ ወቅት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዑመር ሸሪፍ እና የባንባሲ HDSS አስተባባሪ አቶ ድሪባ ኢታና ከክትትል ቡድኑ ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴዎች፣ ውጤቶች እና ቀጣይ እቅዶች አቅርበዋል።
ዶ/ር ዑመር ሸሪፍ የክትትል ቡድኑን በመቀበል ስለ HDSS ፕሮጀክቱ እስካሁን የተከናወኑ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶች ገለጻ ሰጥተዋል።
የክትትል ቡድኑ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ባንባሲ HDSS ጣቢያ ከፍተኛ የሆነ የስራ አፈጻጸም እያሳየ መሆኑን በማድነቅ፣ የታቀዱ ግቦችን በተሳካ ሁኔታ ከማሳካት ባለፈ ለሌሎች HDSS ጣቢያዎች አርአያ ሊሆኑ የሚችሉ የስራ ልምዶችን መፍጠሩን ገልጿል።
ቡድኑ ከዘጠኝ ወራት በፊት ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጉን በማስታወስ፣ በዚህ ጊዜ ያደረገው ግምገማም ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቱን በብቃትና በውጤታማነት እየመራ መሆኑን እንዳረጋገጠ አስታውቋል።
በቀጣይም የፕሮጀክቱን ውጤታማነት ለማጠናከር ለመረጃ ሰብሳቢዎች በፆታ ጉዳዮች ላይ የተመሰረቱ ስልጠናዎችን ማዘጋጀት፣ የHDSS መረጃዎችና ውጤቶች ለምርምር በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ በዩኒቨርሲቲው ዋና ድረ-ገጽ ስር የተለየ የHDSS ድረ-ገጽ ማቋቋም፣ የፕሮጀክቱን የገንዘብና የአሠራር ዘላቂነት ለማረጋገጥ ተገቢ የዘላቂነት ስልቶችን መንደፍ፣ የHDSS ስራዎችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለማስፋፋት ተጨማሪ የክትትል ጣቢያዎችን የመክፈት አማራጮችን ማጤን በዉይይቱ የቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ናቸዉ፡፡
በውይይቱ ወቅት ዶ/ር ዑመር ሸሪፍ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከHDSS ፕሮጀክት ባሻገር ስትራቴጂያዊ አጋርነቶቹን እያሰፋ መሆኑን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው በአሁኑ ወቅት ከአውሮፓ ህብረት፣ ከኢጋድ፣ ከማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ከሌሎች በርካታ ተቋማት ጋር በትብብር የተለያዩ የምርምርና የልማት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም ዩኒቨርሲቲው ያሉትን አጋርነቶች በማጠናከር እና HDSSን ጨምሮ በሁሉም የልማት ዘርፎች ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et