

ፕሬዝዳንቱ በ4ተኛዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባዔ ላይ ገለፃ ለማቅረብ እና በዘርፉ ያላቸዉን ከፍተኛ ልምድ ለማካፈል በስፍራው ለተገኙ ክቡር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በጽ/ቤታቸዉ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።
አሶሳ ዩኒቨርስቲ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለይም ከአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ጋር በህዳሴ ግድብ እና በተለያዩ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች ወይይት ያደረጉ ሲሆን ወደፊት በጋራ የሚሰሩ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል። ዶክተር ያሬድም በዚህ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ለመገኘት በመምጣቸዉ በዩኒቨርስቲው ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዉላቸዋል ።