Assosa University

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ ለክቡር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አቀባበል አደረጉላቸው

ፕሬዝዳንቱ በ4ተኛዉ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባዔ ላይ ገለፃ ለማቅረብ እና በዘርፉ ያላቸዉን ከፍተኛ ልምድ ለማካፈል በስፍራው ለተገኙ ክቡር አምባሳደር ዘሪሁን አበበ በጽ/ቤታቸዉ አቀባበል አድርገዉላቸዋል።

አሶሳ ዩኒቨርስቲ ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለይም ከአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል ጋር በህዳሴ ግድብ እና በተለያዩ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች ወይይት ያደረጉ ሲሆን ወደፊት በጋራ የሚሰሩ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል። ዶክተር ያሬድም በዚህ አለም አቀፍ ኮንፈረንስ ለመገኘት በመምጣቸዉ በዩኒቨርስቲው ስም ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዉላቸዋል ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *