



አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር፣ በስራ ባህል ዕድገትና ምርታማነት ዙሪያ ለክልሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ቁምላቸው አለሙ ሲሆኑ እንደ ሀገር በአገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ ሊሻሻሉ የሚገባቸዉ የአሰራር ዘየወዎች እንዳሉ ገልፀዉ ከዚህ ዉስጥ የስራ ባህል አንዱ በመሆኑ መቀየርና ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡
አዲስና ተጨባጭ የስራ ባህል በመገንባት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ እንዲሁም ለዜጎች ምቹ የስራ ምህዳር ለመፍጠር ሁሉም አመራሮች አሻራቸውን ማሳረፍ እንደሚገባ ዶ/ር ቁምላቸው አሳስበዋል፡፡
የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ስምሪት ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አለነ በበኩላቸው በማንኛውም የስራ መስክ የተሰማሩ አመራሮች ያላቸውን አቅም በአግባቡ በመጠቀም ግንባር ቀደም ሆነው ለዘላቂ የስራ ባህል ዕድገትና ምርታማነት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም እንደ ሀገር፣ እንደ ግለሰብ እና እንደ ተቋም መለወጥ እንደሚቻል በተግባር መረዳት እንደሚገባ ጠቁመው፣ በምንሰራቸው ስራዎችና በእየተቋማችን ለውጥ በማምጣት የስራ ባህልን ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡
የክልሉ ማህበረሰብ የአካባቢውን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ጸጋዎች በአግባቡ በመጠቀም ማህበረሰቡ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችልበት አቅጣጫ በጥናት የተደገፈ ስራ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር ዶ/ር ተፈራ ተሾመ ዩኒቨርሲቲዉ በክልሉ ውስጥ በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዉ ይህ መስል የግንዛቤ ስልጠና በመተከል እና ከማሽ ዞኖች እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#