


የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ እስከ አሁን ከዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ከተማሪ አደረጃጀት አመራሮች እንዲሁም ከአካባቢዉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ከአካሄዷቸዉ ዉይይቶች በመነሳት በመማር ማስተማር፣በአስተዳደር እና ልማት እንዲሁም በምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ቅድሚያ ተሰጥቷቸዉ ሊሰሩ የሚገባቸዉን የአጭር እና የረዥም ጊዜ የትግበራ እቅድ በዛሬዉ ዕለት ለመምህራን አቅርበዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።
የመነሻ ዕቅዱም በዚህ በጀት አመት ማጠናቀቂያ እና በ2019 በጀት ዓመት በክረምት ወቅት እና በቀጣ ጊዜያት ትኩረት ተሠጥቷቸዉ የሚሰሩ ሥራዎችን በትግበራ እቅድ(Action Plan)መልክ ለዉይይት መነሻነት ቀርበዋል።
ዉይይቱ ያስፈለገበትም ዋነኛ ዓላማ ትኩረት የሚያስፈልጋቸዉ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷቸዉ እንድሠሩ እና ሁሉም ለዕቅዱ ስኬት የድርሻዉን እንድወጣ ለማድረግ እንደሆነ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ገልጸዋል።
ዶ/ር ያሬድ በትግበራ እቅዱ ላይ በክረምት ትኩረት ተሠጥቷቸዉ ይሰራሉ ብለዉ ካነሷቸዉ ሥራዎች መካከል የICT መሠረተ ልማት ማስፋፋት፣ግንባታቸዉ በመጠናቀቅ ላይ ያሉ ህንጻዎችን አጠናቆ ማስመረቅ፣የተማሪዎች መኝታ ቤቶችን ማደስ እና የዉሃ እንዲሁም የመብራት አገልግሎቶችን ማሟላት የሚሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ።
በቀጣይነትም ኢንተርፕራይዝ በመፍጠር የዉስጥ ገቢን ማሳደግ፣የተማሪዎችን ቁጥር መጨመር፣የሥርዓተ ትምህርት ክለሳ፣የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማጠናከር፣የትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ እና አዳዲስ ስልጠና ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ትኩረት ተሰጥቶባቸዉ ከሚሰሩ ሥራዎች መካከል እንደሆኑ ገልጸዋል።
የዉይይቱ ተሳታፊ መምህራንም ለመሥራት የታቀደዉ የትግባራ ዕቅድ ከዚህ በፊት ሲካሄዱ በነበሩ የዉዉይት መድረኮች እንዲሠሩ ስንጠይቃቸዉ የነበሩ በመሆናቸዉ አሁንም ትኩረት ተሠጥቶባቸዉ እንድሠሩ ከጠየቁ በኋላ ለተግባራዊነታቸዉ የድርሻቸዉን እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም መምህራን የሚያነሷቸዉን ጥያቄዎች የዩኒቨርሲቲዉ ማኔጅመንት ለፌዴራል እና ለክልል የመንግስት አካላት የሚቀርቡትን መልስ እንዲያገኙ እንደሚሠራባቸዉ በመግባባት ዉይይቱ ተጠናቋል
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ
For Additional Information
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et