


የዩኒቨርሲቲዉ ሴኔት ዛሬ ባካሄደዉ ስብሰባ በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ መሪነት የ2018 ዓ.ም የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተመራቂ ተማሪዎች ስታተስ ፣የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) እና ነጻ የትምህርት እድል ለማህበረሰቡ የሚሰጥበትን ጉዳዮች ጥልቅ ዉይይት በማድረግ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡
በዘንድሮዉ ዓመት ዩኒቨርሲቲዉ በቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ መርሃ ግብር 673 ተመራቂዎችን እንደሚያስመርቅ የዋናዉ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሸንቁጥ ገልጸዋል፡፡
የመዉጫ ፈተና የማለፍ ምጣኔም በዘንድሮዉ ዓመትም የተሻለ ዉጤት የተመዘገበ ሲሆን የድህረ ምረቃና ቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን ሰኔ 20/2018 ዓ/ም ዩኒቨርስቲው ያስመርቃል።
ሰኔቱ የተወያየው ሌላ ጉዳይ የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ የፀደቀ ሲሆን በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ዩኒቨርስቲው እንደ አፕላይድ ሳይንስ ውጤት ተኮር ስራዎች ላይ እንዲሰራ ሰኔቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ
For Additional Information
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
See less