



አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ትብብር ዕድሎችን እያሰፋ መሆኑን የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ ገለፀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ የማዕድን ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው 2ኛዉ የሩሲያ-አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የጥሬ ሀብት ውይይት መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፡፡
በአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ጥሪ መሠረት አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በዚህ አለም አቀፍ ዉይይት መድረክ የተሳተፈ ሲሆን ከጉባኤዉ ጎን ለጎን ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ፕሬዚዳንት፣ ከአፍሪካ እና ሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዘዳንቶች ጋር በተለያዩ የትብብር ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይቶችን ማድረጋቸዉን ዶ/ር ያሬድ ተናግረዋል፡፡
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (University of Applied Sciences) እንደመሆኑ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበራት ጋር በትብብር ለመስራት በሚቻልባቸዉ ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቅ መወያየታቸዉን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ በጥናትና ምርምር፣ በመምህራንና ተማሪዎች ልውውጥ፣ በዓለም አቀፍ የጋራ ኮንፈረንሶች እና ሰሚናሮች ዝግጅት እንዲሁም ሌሎች አካዳሚያዊ ተግባራት ዋና ዋናዎቹ እንደ ነበር አብራርተዋል።
ዩኒቨርሲቲዉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መዲና እንደሚገኝና በክልሉ ያለውን የማዕድን ሀብት እና ስትራቴጂያዊ ፋይዳ እንዲሁም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) መገኛ ያሉበት መሆኑን በጉባኤዉ ላይ ለተገኙ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች አለም አቀፍ አጋር አካላት ማብራራታቸዉን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ በጉዳዩ ላይ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዩኒቨርሲቲዉን በጎበኙበት ጊዜ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት የማዕድን ኢኒስቲትዩት (Mining institute) ለማቋቋም እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ያሬድ ይህም በዘርፉ የሚካሄደው የጥናትና ምርምር፣ ፈጠራ እና የሰው ኃይል ልማትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በጥናትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አንስተዉ ዘርፉን ለማስፋት ዩኒቨርስቲዉ ቁርጠኛ መሆኑን ጎን ለጎን በተካሄዱ ዉይይቶች ገለፃ ማድረጋቸዉን ገልፀዋል፡፡
ውይይቱ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲን አቅም በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅ እና ዓለም አቀፍ የትብብር አጋርነቶችን ለማስፋት ጠቃሚ እድል እንደፈጠረላቸዉ ያወሱት ፕሬዚዳንቱ ከማህበራቱ ጋር በቀጣይ ጊዜያት ውይይቶች፣ ተቋማዊ ጉብኝቶች እና በጋራ ፍላጎቶች ትብብራቸውን ለማጠናከር ትኩረት እንደሚሰጥ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል።
ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et