የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ እና የማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሲሳይ በቀለ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ጉዳዮች ዙሪያ የሥራ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ እንደገለጹት፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የመምህራንን ሙያዊ ሚና ማጠናከር፣ የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ የመምህራን ማህበርን እንቅስቃሴ ማሳደግ፣ እንዲሁም የመምህራንን የሥራ ሁኔታና የሙያ ጥቅሞች ለማሻሻል በጋራ የሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ ገንቢ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።
ዶ/ር ያሬድ አክለውም፣ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ መምህራንና የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በቅርበት ተባብረው መሥራት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ መግባባት መደረሱን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደመላሽ መንግስቱ በበኩላቸው፣ ማህበሩ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅርበት በመተባበር የመምህራንን ሙያዊ እድገት ለማጎልበት፣ የሥራ አካባቢን ለማሻሻል እና የዩኒቨርሲቲውን አጠቃላይ አፈጻጸም ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሠራ አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም በጋራ በመሥራት የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማሻሻል፣ የመምህራንን ጥቅም ለማስጠበቅ እና የዩኒቨርሲቲዎችን ተልዕኮ በተሻለ ሁኔታ ለማሳካት የቅርብ ትብብር እንደሚያደርጉ በመግለጽ ውይይታቸውን አጠናቀዋል።
ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029