
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁ ተማሪዎችን ሰኔ 20/2018 ዓ.ም. በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የላቀ የትምህርት ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት የተሰጣቸው ሲሆን፣ ከፋርማሲ ትምህርት ክፍል 3.98 የውጤት ነጥብ (CGPA) በማስመዝገብ የተመረቀው ተማሪ ኪዳነማርያም ውለታው የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የአካዳሚክ ውጤት ባለቤት በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።
ተማሪ ኪዳነማርያም ከምረቃው በኋላ ለዩኒቨርሲቲው የሚዲያ ቡድን በሰጠው አስተያየት፣ ይህን የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የቻለው ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም፣ በትጋት እና በተከታታይ በማጥናት መሆኑን ገልጿል።
በተጨማሪም ለዚህ ስኬት መድረሱ የቤተሰቡ፣ የመምህራኑና የወዳጆቹ ድጋፍና ማበረታቻ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሷል።
በመጨረሻም ለሌሎች ተማሪዎች ባስተላለፈው መልዕክት፣ ግብ በማስቀመጥ፣ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም እና በተከታታይ ጥረት በማድረግ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ገልጾ፣ ሁሉም ተማሪዎች በትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስቧል።
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ
For Additional Information
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et