




አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምሩቃን ቅጥር ዕድል ለማስፋት የሚያስችል ከቀጣሪ ድርጅቶች እና ኢንዱስትሪዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል።
እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ተግባር ተኮር የትምህርት ፕሮግራሞችን በመክፈት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት በትጋት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዶ/ር ያሬድ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ተቋማት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በመፈራረም ወደ ተግባራዊ ሥራ መግባት እንደሚገባው ገልጸው፣ ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ብቃት ያለው ትውልድ ለማፍራት የሁሉም አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።
በውይይቱ ላይ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክተር ዶ/ር ገለታ ፍቃዱ የመነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀረበው ፅሁፍ ላይ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርበዉ በተነሱ ሀሳቦች ላይ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ በሆኑት በዶ/ር ወንድም መኩሪያ እና በአስተዳደር ልማት ም/ፕሬዚዳንት በዶ/ር አቢዮት አበጀ ምላሽ እና ማብራሪያዎች ተሰጥቷል።
በዉዉይቱ ቀጣሪ ድርጅተቶች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና የክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱ ምሩቃንን ከሥራ ዕድሎች ጋር በቅርበት ለማገናኘት እና የዩኒቨርሲቲና ኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።