Assosa University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምሩቃን ቅጥር ዕድል ለማስፋት ከቀጣሪ ተቋማትጋር ውይይት አካሄደ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምሩቃን ቅጥር ዕድል ለማስፋት የሚያስችል ከቀጣሪ ድርጅቶች እና ኢንዱስትሪዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

‎በመድረኩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ በመሆኑ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር በትብብር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

‎እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ተግባር ተኮር የትምህርት ፕሮግራሞችን በመክፈት ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ለማፍራት በትጋት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎ዶ/ር ያሬድ በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ ተቋማት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን በመፈራረም ወደ ተግባራዊ ሥራ መግባት እንደሚገባው ገልጸው፣ ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ብቃት ያለው ትውልድ ለማፍራት የሁሉም አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

‎በውይይቱ ላይ በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ማሻሻያ ዳይሬክተር ዶ/ር ገለታ ፍቃዱ የመነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ በቀረበው ፅሁፍ ላይ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶችን አቅርበዉ በተነሱ ሀሳቦች ላይ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳይ ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ በሆኑት በዶ/ር ወንድም መኩሪያ እና በአስተዳደር ልማት ም/ፕሬዚዳንት በዶ/ር አቢዮት አበጀ ምላሽ እና ማብራሪያዎች ተሰጥቷል።

‎በዉዉይቱ ቀጣሪ ድርጅተቶች፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና የክልሉ ሴክተር መስሪያቤቶች በመድረኩ የተሳተፉ ሲሆን ውይይቱ ምሩቃንን ከሥራ ዕድሎች ጋር በቅርበት ለማገናኘት እና የዩኒቨርሲቲና ኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *