በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናከር እንዲሁም የባህል ልውውጥን ዓላማ ያደረጉ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የአሶሳ ዩኒቨረትሲቲ የምርምር፣ ህትመት ስነምግባርና ስርጸት ዳይሬክተር ዶ/ር ዑመር ሸሪፍ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሔረሰቦች መገኛ ሀገር መሆኗን በማስታወስ ባህላችንን በአግባቡ መጠበቅ፣ ማክብር፣ ማልማት እና መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አክለዉም ኪነ-ጥበብ በሀገራችን እና በዩኒቨርሲቲው የልማት ዕቅድ ውስጥ አስፈላጊ ሚና እንዳለው ገልፀዉ በጥበብ አማካኝነት ትውልድን ማስተማር፣ ጥበብን የአዕምሮ ልማት መሳሪያ ማድረግ፣ ባህላችንን በጥናት መለየት እና ባህላዊ እሴቶቻችንን ለወጣቱ ትዉልድ በትክክል ማስተላለፍ አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ ግጥም፣ የባህላዊ አልባሳት ትርዒት፣ ባህላዊ ውዝዋዜዎችና ‘’አወር እና እፁ’’ የተሰኘ ትውፊታዊ ተውኔት ቀርበዋል።
ተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et




