Assosa University

3ኛዉ የተግባር ተኮር( Applied science Universities) የጋራ ፎረም የወደፊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቀቀ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተካሄደዉ የ 15 ቱ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ ፎረም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ዉጤታማ ዉይይት በማድረግ እና የወደፊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ዛሬ ተጠናቋል።
‎ በፎረሙ ላይም የተግባር ተኮር ዩኒቨርሲቲዎች ሥርዓተ ትምህርት ክለሳ ሂደት እና ተግዳሮት ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ፣ትልልቅ ፕሮጀክቶችን የማፈላለግ እና የማስተዳደር ምርጥ ተሞክሮ እንዲሁም የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በትኩረት መስክ ልየታዉ መሠረት የሠራቸዉ ሥራዎች ተሞክሮ እና ልምድ ቀርበዉ የጋራ ዉይይት ተደርጎባቸዋል።
‎ከዉይይቱ ጭብጥ በመነሳትም የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ በሚያደርጓቸዉ ጉዳዮች የጋራቸዉን ወስደዉ ወደየእራሳቸዉ ፀጋዎች የሚያተኩር ሥርዓተ ትምህርት ማተኮር እንዳለባቸዉ እና ከኢንዱስትሪዎች ጋር ተባብረዉ መሥራት እንደሚጠበቅባቸዉ በማለት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን እና የጋራ ስምነት የተደረሰባቸዉ ነጥቦችን የቀጣይ አቅጣጫ አድርጎ በማስቀመጥ ፎረሙ ተጠናቋል።
‎የፎረሙ አባላት አሶሳ ዩኒቨርሲቲ እንደ አዘጋጅ ዩኒቨርሲቲ ዉጤታማ እና ስኬታማ የሆነ ፕሮግራም በማዘጋጀቱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሠማቸዉ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *