Assosa University

ዩኒቨርሲቲዉ ለመምህራን እና ለትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና መሰጠት ጀመረ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እና ከቤ/ጉ/ክ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከሐምሌ 28/2017 ዓ/ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዉ ለ2ኛ ዙር የሚሰጠዉን የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልዩ የክረምት አቅም ግንባታ ስልጠና ተጀምሯል፡፡
 
የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ ረዳትና የም/ፕሬዚዳንቱ ተወካይ ዶ/ር አቢዮት አበጀ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እንደ ሀገር ከያዛቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀዉ ለዚህም የመምህራንን እና የትምህርት አመራሩን አቅም ማጎልበት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
 
የስልጠናዉ ዓላማም የመምህራንን እና የትምህርት አመራሩ ላይ የዕዉቀትና ክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።
 
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የስልጠናው ዋና አስተባባሪ መ/ር ደረጀ አክሌ እንደገለፁት ስልጠናው በሀገር ደረጃ በ30 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ጠቅሰው በዩኒቨርሲቲዉም 106 የት/ቤት አመራሮች እና 458 መምህራን በአጠቃላይ 564 በላይ ሰልጣኖች እንደተመደቡ ተናግረዋል፡፡
አክለዉም ሰልጣኞች በዩኒቨርሲቲዉ በሚኖራቸው የስልጠና ቆይታ የተሻለ እውቀትና ክህሎት ይዘው እንዲወጡ ለማስቻል በቂ ዝግጅት መደረጉንም ገልጸዋል።
 
ስልጠናዉ ከሐምሌ 28/11/2017 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 22/2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚቀጥል በወጣዉ የሥልጠና መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡
 
ተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X (https://x.com/AssosaU)
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *