Assosa University

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አሻዲሊ ሀሰን በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት አደረጉ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ አሻዲሊ ሀሰን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ ሐምሌ 17/ 2018 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጉብኝት በዩኒቨርሲቲው እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋዉሮ የተመለከቱ ሲሆን የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ዩኒቨርሲቲው የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ በዩኒቨርሲቲዉ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ሲሆን ከነዚህም መካከል የተማሪዎች መኝታ ቤት (Students Dormitory) ማዘመን ሥራ አንዱ ነበረ። በዚህም ረገድ ዩኒቨርሲቲዉ የቤት ሥራዉን ከወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ቀን ከሌሊት ርብርብ እያደረገ ይገኛል። ክቡር ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻዲሊ ሀሰን ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ እና ሌሎች የክልሉ እና የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ጋር በመሆን የእድሳት ሥራዉን ተዘዋዉሮ ጎብኝተዋል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻዲሊ ሀሰን ከጉብኝት መልስ የአረንጓዴ አሻራቸዉን በማስቀመጥ ከዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ ጋር አብሮ በሚሠሩ ሥራዎች ዙሪያ ዉይይት አድርጓል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሀገሪቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ያሉበት እና ለልማት ተስማሚ መልከዓ ምድር የተጎናፀፈ እንደሆነ በመድረኩ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ማህበረሰቡ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ከዩኒቨርሲቲዉ ጋር ተቀራርቦ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲዉ ከመማር ማስተማር ሥራዉ ባሻገር በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎቹ ክልሉን እንዲያግዝ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ለተደረጉላቸዉ አቀባበልም ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ በበኩላቸዉ ክቡር ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻዲሊ ሀሰን ዩኒቨርሲቲውን መጎብኘታቸውን አመስግነዉ ዩኒቨርሲቲዎች በአንድ አከባቢ ላይ ሲቋቋሙ ለአካባቢዉ ማህበረሰብ ልማት እንዲያግዙ ታስቦ መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህ ረገድም ከዩኒቨርሲቲዉ ሰፊ ሥራ ይጠበቃል ያሉት ዶ/ር ያሬድ ዩኒቨርሲቲዉ ባለዉ አቅም ከክልሉ ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራ ቃል ገብቷል። የክልሉ መንግሥትም በሚንፈጋቸዉ ጊዜ ሀሉ ከዩኒቨርሲቲዉ ጎን እንዲሆን ጭምር ጠይቋል።

ፕሬዝዳንቱ በኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ሓላፊነት ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተመድበዉ ሥራ በጀመሩበት ወቅት ከክቡር ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻዲሊ ሀሰን ጋር ዉይይት ማድረጋቸዉ ይታወሳል።

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

Website: www.asu.edu.et

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *