Assosa University

ዙምባራ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኀብረት ሥራ ማኅበር የምስረታ እና መተዳደሪያ ደንብ ገለፃ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተደረገ

ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም

ዙምባራ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማህበር በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች  እና መምህራን የጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ማህበር ነው። የህብረት ሥራ ማህበሩ ዓላማ የአባላቱን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መደበኛና የፍላጎት ቁጠባን እና የተለያዩ የብድር አገልግሎቶችን በመስጠት የኢንቨስትመንት አቅም በማጎልበት ጠንካራ የፋይናንስ ተቋም ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ ነው::

የዙምባራ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ ኅብረት ሥራ ማኅበር አባላትም በዛሬው ዕለት የማህበሩ ስያሜ፣ ወርሃዊ ክፍያ፣ ለመሸጥ የተዘጋጀ ጠቅላላ ዕጣ እና የአንድ እጣ መሸጫ ዋጋ እንድሁም በመተዳደሪያ ደንብና በብድር መመሪያው ላይ የማሻሻያ ሃሳቦች ላይ  አባላቱ ተወያይቶ ጠቃሚ ውሳኔዎችን አሳልፏል::

“ኑ የራሳችንን ችግር በጋራ እንፍታ”!!

Assosa University Public and International Relations Directorate

Face book: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/assosauniversity_official

Website: https://www.asu.edu.et

Email: pir@asu.edu.et

PoBox 18

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *