



አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።
በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ “እንኳን ወደ ሰላማሙ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ” በማለት ምቹ የትምህርትና የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር የማደሪያ ቤቶችን ማደስ፣ የምግብ ቤትን ማሻሻል፣ የውሃ አቅርቦትን ማሟላትና የትምህርት መርሃ ግብር የክለሳ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በእውቀት፣ በክህሎትና በሥነ ምግባር የታነጹ ዜጎች ሆነው እንዲመረቁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸው፣ መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ለተማሪዎች ማንኛውም ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ፕሬዝዳንቱ ተማሪዎች ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም፣ በትጋት በማጥናትና የነገ ተስፋን በመሰነቅ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አሳስበው ለቅበላው ምቹ ሁኔታ ላመቻቹ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ የክልሉ መንግሥትና የግልገል በለስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ምስጋና አቅርበዋል።
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የአካባቢው ሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ተገኝተው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የማበረታቻና የመልካም ምኞት መልዕክትም አስተላልፈዋል።
ዩኒቨርሲቲው በ2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ፈተና ተፈትነው ያለፉና በቀጥታ የተመደቡ ከ1,430 በላይ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል።
ዩኒቨርሲቲው ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን ይመኛል።
ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ!
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
