Assosa University

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከሴት ተማሪዎች ጋር በየሳምንቱ አርብ ምሽት የሚደርገዉ ዜሮ ፕላን ፕሮግራም ተካሄደ

ፕሮግራሙ የሚዘጋጀው በዩኒቨርሲቲዉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ አስተባባርነት ሲሆን ፕሮግራሙ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የካቲት 07/2017 ዓም ተካሂዷል።
 
በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲዉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ መ/ርት መርቀኒያ አሊ የፕሮግራሙን ዓላማ ሲገልጹ የዩኒቨርሲቲዉ ሴት ተማሪዎች ለተለያዩ መስናክሎች የተገላጭነት መጠናቸውን ወደ ዜሮ ለማውረድ እና በህይወታቸዉ ዉስጥ ሊገጥማቸዉ የሚችሉ ፈተናዎችን በድል ማለፍ እንዲችሉ በቂ ልምድ ያላቸው እና በትምህርታቸው ውጤታማ የሆኑ ተማሪዎች እየተገናኙ ቡና እየጠጡ የሚማማሩበት እና ተሞክሯቸውን የሚያካፍሉበት ፕሮግራም መሆኑን አብራርተዋል።
 
በተጨማሪም መ/ርት መርቀኒያ ሴት ተማሪዎች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ ፣ ከየትኛዉም ዓይነት የአቻ ግፊት እራሳቸዉን መጠበቅ እንዳለባቸዉ፣ ሰዓታቸውን በአግባቡ መጠቀም እና ለትምህርታቸዉ ቅድሚያ በመስጠት ከዓላማቸው ሊያዘናጓቸው ከሚችሉ ተግባራት እንዲጠበቁ ግንዛቤ ለማግኘት እንዲረዳቸዉ ታስቦ የሚዘጋጅ ፕሮግራም በመሆኑ ሁሉም ሴት ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ አሳስበዋል ።
 
የአሶሳ የኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ም/ፕሬዝዳንት የሆኘችዉ ተማሪ ጥሩዓይነት ዜሮ ፕላን ፕሮግራም ሴት ተማሪዎች እርስ በእርስ በመማማር የተጋላጭነት መጠናቸውን ዝቅ ለማድረግ ብሎም ዜሮ ደረጃ ላይ የሚያደርሱበት ፕሮግራም ከመሆኑ በተጨማሪ ሴት ተማሪዎች የይቻላልን መንፈስ የሚያጎናፅፍ ፕሮግራም መሆኑን በመግለጽ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለዉ ገልጻለች።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *