የሰላም ሚኒስቴር ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ13ኛ ዙር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰልጣኞች የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ።
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት እና የዕለቱ የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ዶ/ር ጌታቸዉ አለሙ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ” ከተለያዩ ቦታዎች ተሰባስባችሁ የመጣችሁ ወጣቶች በስልጠና ቆይታችሁ ኢትዮጵያዊ ባህሎቻችንን፣ ቋንቋዎችን እና እሴቶቻችንን በመጋራት ሀገራዊ ሕብር የምታጠናክሩበት” ነዉ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዶ/ር ጌታቸዉ አክለዉም ሰልጣኞች በዩኒቨርሲቲዉ በሚኖራቸዉ የስልጠና ቆይታ አስፈላጊውን ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
በስልጠና ማስጀመሪያ መርሃግብር የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ አምባሳደር እሸቱ ደሴ “በበጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ሥራ ላይ መሳተፍ የህሊናና የመንፈስ እርካታ የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ ስልጣኞች በሀገራዊ መግባባት ሥራ ውስጥ የራሳችሁን አዎንታዊ አሻራ በማሳረፍ የዜግነት ግዴታን መወጣት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
መርሐ ግብሩ የወጣቱን አመለካከት፣ ክህሎትና ሞራል በመገንባት እንዲሁም አንዱ የሌላውን ባህልና እሴት እንዲገነዘብ በማድረግ ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር እና ለሀገራችን ሰላምና አንድነት መጠናከር የጎላ ሚና ያለው መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የክልሉ ፀጥታና ሰላም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግስቱ ላሎ በበኩላቸዉ በጎ ፍቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ሰልጣኖች እርስ በርዕስ በመተዋወቅ እና በመረዳዳት ከተለያዩ የሀገራችን ክፍል የሚገኙ ባህሎችንና ዕሴቶችን የምታውቁበት ፕሮግራም ነው ብለዋል። በመጨረሻም ስልጠና በዩኒቨርሲቲዉ ለተከታታይ 22 ቀናት እንደሚሰጥ ተገልፃል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#