Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መሥጠት ተጀመረ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መስጠት ተጀምሯል።

ከዛሬ ሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 16/ 2018 ዓ.ም የሚሰጠዉ ይህ የሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በበይነ-መረብ እና በወረቀት በስድስት ዙር የሚካሄድ ሲሆን የመጀመሪያው በበይነመረብ (Online) ተፈታኝ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸዉን እየወሰዱ ይገኛሉ።

የፈተና አጀማመሩን የዩኒቨርሲቲዉ እና የቤ/ጉ/ክ ከፍተኛ አመራሮች ተዘዋውሮ የተመለከቱ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር በበይነመረብ ተፈታኝ ተማሪዎች ያለምንም ችግር ፈተናቸዉን እየወሰዱ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዚህ በ2018 ዓ.ም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ 5195 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና እንደሚወሰዱ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዘዳንት ተወካይና የፈተና ማዕከሉ አስተባባሪ ዶ/ር ወንድም መኩሪያ የገለፁ ሲሆን ከነዚህም 1955 ተማሪዎች በበይነመረብ ለፈተና የሚቀመጡ እንደሆነ አብራርተዋል። ዛሬ ሰኔ 23/ 2018 ዓ.ም በመጀመሪያ ዙር ብቻ 207 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸዉን በመዉሰድ ላይ መሆናቸዉን ጭምር ዶ/ር ወንድም ገልጸዋል።

ስለ ዩኒቨርሲቲዉ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

Website: www.asu.edu.et

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *