Assosa University

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ተጀመረ

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ተጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ፣ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት በርካታ ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ልማት አስፈላጊ አስተዋፅኦ ማድረጉን አስታውሰዉ በቀጣይም የዩኒቨርሲቲውን አረንጓዴ አሻራ በማጠናከር የአካባቢና የአፈር ጥበቃ ሥራዎችን ማስፋፋት ከተቋሙ የሚጠበቅ ዋና ሀላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንቱ አክለውም፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የታላቁ የህዳሴ ግድብ መገኛ በመሆኑ የአካባቢ ጥበቃና የተፋሰስ ልማት ሥራዎችን በማጠናከር ግድቡን ከደለልና ከጎርፍ አደጋ ለመጠበቅ የሁሉም ተቋማትና ዜጎች ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው፣ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ በተግባር መደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የማህበረሰብ ጉድኝ ዳይሬክተር ዶ/ር ተፈራ ተሾመ በበኩላቸዉ ፣ የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል በሀገርና በክልል ደረጃ መጀመሩን አስታውሰው፣ በዩኒቨርሲቲውም ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሰፊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መጀመሩን ገልጸዋል።

በዕለቱ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ ሠራተኞች እንዲሁም የ2018 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።

በመርሃ ግብሩ የዩኒቨርሲቲዉን አረንጓዴ ውበት የሚያጎለብቱ እንዲሁም ለምግብና ለኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚውሉ የተለያዩ የፍራፍሬና የጥላ ዛፍ ችግኞች ተተክለዋል።

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራምን በቀጣይነት በማስፈጸም ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአፈርና ውሃ ሀብት ጥበቃ እንዲሁም ለዘላቂ ልማት ያለውን አስተዋፅኦ ይበልጥ ለማጠናከር እየሠራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ

‎For Additional Information

‎Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

‎Website: www.asu.edu.et

‎WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

‎Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

‎Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

‎Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *