Assosa University

ዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት የተማሪዎችን ምኝታ ቤቶች ዕድሳት አስጀመሩ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ሙሉ የተማሪዎችን ምኝታ ቤቶች ምቹ፣ ንጹህና ማራኪ ለማድረግ የታቀደውን ሙሉ የዕድሳት ሥራ ዛሬ በይፋ አስጀምረዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፣ የተማሪዎችን የመኖሪያ ሁኔታ ለማሻሻልና ለትምህርት ምቹ አካባቢ ለመፍጠር የተጀመረው የምኝታ ቤቶች የዕድሳት ሥራ በክረምት ወቅት ተጠናቆ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ እንደሚሆን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሥራው በተያዘለት ጊዜና በተፈለገው ጥራት እንዲጠናቀቅ ልዩ የክትትል ኮሚቴ መዋቀሩን ጠቅሰው፣ ሁሉም የዕድሳት ሥራዎች በተገቢው ደረጃና ጥራት እንዲከናወኑ አሳስበዋል።

በዕድሳት ፕሮጀክቱ ውስጥ የሲራሚክ ንጣፍ ማንጠፍ፣ የኮርኒስ ቅየራ፣ የመብራት ሥርዓት ማሻሻያ፣ የውስጥና የውጭ ቀለም ሥራዎች እንዲሁም ሌሎች አጠቃላይ የጥገና ሥራዎች የሚከናወኑ ሲሆን፣ የግቢ ውበት ማሻሻያ ሥራዎችም እንደሚካተቱ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንቱ ከዚህ ቀደም ከመምህራንና ከሠራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የተማሪዎች ምኝታ ቤቶች ጥገናና የግቢ ውበት ማሻሻያ ሥራዎች ዩኒቨርሲቲው ቅድሚያ ከሰጣቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል አንዱ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። በዚህም መሠረት ሥራዎቹ በተቀናጀና በተጠናከረ መንገድ እንደሚፈጸሙ አስታውቀዋል።

የዕድሳት ሥራው ሲጠናቀቅ ለተማሪዎች የተሻለ የመኖሪያ ምቾት ከመፍጠሩ ባሻገር፣ የዩኒቨርሲቲውን አጠቃላይ ገጽታና የግቢውን ውበት በእጅጉ በማሻሻል ለተሻለ የትምህርትና የመኖሪያ አካባቢ መፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *