Assosa University

በተግባራዊ ምርምርና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነዉ

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤ/ጉ/ክ/መ/ ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር ለቴክኒክና ሙያ እና ለግል ኮሌጅ መምህራን በተግባራዊ ጥናትና ምርምር፣ በሀገር በቀል የሙያ ዕውቀትና ክህሎት፣ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናውን የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል የከፈቱ ሲሆን፣ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከክልሉ ተቋማት ጋር በመተባበር በርካታ ልማታዊ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዉ ከክልሉ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸዉን አስታዉሰዉ የዛሬዉ ስልጠናም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህ የቅንጅት ስራም የሀገር ልማትን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው የአሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ለማሻሻል፣ የአገር በቀል ዕውቀትን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር በተግባር ላይ ለማዋል እንዲሁም የምርምር ውጤቶችን ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም አቶ አብዱሰላም ጠቁመዋል፡፡

በስልጠናው ላይ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዑመር ሸሪፍ በእኳን ደህና ካሉ በኋላ ዩኒቨርሲቲዉ ከሀገር ውስጥና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነዶችን በመፈራረም በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ከእነዚህ ተግባራት መካከል አንዱ ይህ ለአሰልጣኞች የተዘጋጀው ስልጠና መሆኑን ጠቁመው፣ ዩኒቨርሲቲው በክልሉ በትምህርት፣ በግብርና፣ በጤና፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እና በሀገር በቀል ዕውቀት ዙሪያ በጥናትና ምርምር በመለየትና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ስልጠናው ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ቀን በዶ/ር አልማዝ ደቼ በሀገር በቀል የሙያ ዕውቀትና ክህሎት ላይ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *