






የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የቃልኪዳን ቤተሰብ የምሥረታ መርሃ-ግብር እና የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን ከአሶሳ ከተማ ማህበረሰብ ጋር የማረካከቢያ ዝግጅት በዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ሲሆኑ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ዩኒቨርሲቲዉ ከተቋቋመ ጀምሮ ላለፉት 14 አመታት አመታት በርካታ እገዛዎችን እያደረገ ያስተማራቸዉ ተማሪዎች በታላላቅ ተቋማት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
የዛሬው የቃል ኪዳን ቤተሰብ ትስስር ምስረታም ዩኒቨርሲቲውና የከተማው ማህበረሰብ በጋራ በመስራት የእንግዳ ተቀባይነት ባህላችንን በማዳበር ተማሪዎቻችን ሲመጡ ያለንን መልካም ባህል፣ እሴቶችና፣ ጸጋዎችን አሳውቀናቸው በሚሄዱበት አካባቢ ሁሉ አምባሳደር እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡
እንዲሁም ተማሪዎቹ ከዩኒቨርሲቲው አልፈው የአካባቢውን ማህበረሰብ እንደቤተሰባቸው በማየት ባይተዋርነት ሳይሰማቸው ትምህርታቸውን በስኬት እንዲያጠናቅቁ ሚናው የጎላ ነው ሲሉ ዶ/ር ከማል ተናግረዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ሰላም ፀጥታ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ክቡር አቶ አህመድ የሱፍ በበኩላቸዉ የከተማዉ ማህበረሰብ እንግዳ ተቀባይና ሠላም ወዳድ ማህበረሰብ መሆኑን ገልፀዉ የዩኒቨርሲቲዉን ተማሪዎች እንደ ቤተሰብ በማየት ያለምንም ስጋት ትምህርታቸዉን ተከታትለዉ እንዲጨርሱ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎች ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ ምንም ስጋት ሳይኖራቸዉ እንደሁለተኛ ወላጅ በመሆን ሁሉም የከተማዉ ማህበረሰብ የበኩሉን መወጣት እንዳለበትም አቶ አህመድ አሳስበዋል፡፡
በቃልኪዳን ቤተሰብ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ከማል አብዱራሂም እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች እያንዳንዳቸው 1 የቃልኪዳን ልጆችን የተቀበሉ ሲሆን የከተማ አሰተዳደሩ ሃላፊዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች እና በፕሮግራሙ የተገኙ እንግዶችም የቃልኪዳን ተማሪዎችን ተረክበዋል፡፡
በመጨረሻም ተሳታፊዎቹ ተማሪዎችን መደገፍ ሀገርን የመገንባት ስራ እንደሆነ ገልጸው፤ ተማሪዎቹ በመልካም መሰረት ታንጸው ጥሩ ሀገር ተረካቢ እንዲሆኑ ተማሪዎችን ተቀብለን ተንከባክበን አስተምረን ለማስመረቅ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Website: www.asu.edu.et
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et