Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እዉቅና ተሰጣቸዉ

የእዉቅና አሰጣጥ መርሃግብሩ የተካሄደዉ ከ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ ጀምሮ አስከ ተመራቂ ተማሪዎች በሰባቱ ኮሌጆች በእንዳንዱ ባች አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ከፍተኛ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የሰርትፊኬት እና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዉ ለተማሪዎቹ የእዉቅና ሰርትፊኬቱን ያበረከቱ ሲሆን ተማሪዎቹ አሁን ያስመዘገቡትን ዉጤት በሀገራዊ መዉጫ ፈተና እንድደግሙት አሳስበዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ አያይዘዉም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ እስካሁን ካስመረቃቸዉ ምሩቃኖች መካከል በተለያዩ መስኮች ተሰማርተዉ የዩኒቨርሲቲዉን ስም በማስጠራት ላይ ያሉ ምሩቃንን አፍርተናል እናንተም ለዚህ ዉጤታማነት በመብቃታችሁ በእጅጉ ተደስተናል፡፡ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

በተመሳሳይም በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙ የኮሌጅ ድኖች እና ዳይሬክተሮች ለተሸላሚ ተማሪዎቹ ምክር እና የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችን ይከተሉ

Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X

Website: www.asu.edu.et

WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P

Facebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial

Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk

Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *