Assosa University

በዩኒቨርሲቲዉ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በተለያዩ መርሐ ግብሮች በድምቀት ተከበረ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ ፤ በኢትዮጵያ ደረጃ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን “የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ ግብሮች በድምቀት ተከብሯል።
 
መርሀ-ግብሩን በንግግር የከፈቱት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብዱልሙህሲን ሀሰን ሲሆኑ ሴቶች በትምህርት፣ በምርምርና በማህበረሰብ ልማት ውስጥ ያላቸው ሚና እጅግ ከፍተኛ በመሆኑገ ልፀዉ በዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራንን፣ ሰራተኞችን እና ተማሪዎችን ለማበረታታት በርካታ ተግባራት እየተከናውኑ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡
 
ለአብነትም ለሴት መምህራን የሚደረጉ ልዩ የምርምር ስልጠናዎችና የጥናትና ምርምር ስራዎች ፣ ሴቶች ወደ አመራር እንዲመጡ የማበረታቻ ሥርዓቶች እና ለሴት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ማዘጋጀትና የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች መስጠት እና ሌሎችም በርካታ ተግባራት እየተሰሩ እንደሚገኙ ዶ/ር አብዱልሙህሲን ገልጸዋል፡፡
 
ለሀገር ሁለንተናዊ ለዉጥ መሪነት ሚና የሚጫወቱ ሴቶችን ማፍራት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚጠበቅ በመሆኑ ሁላችንም ድጋፍና እገዛ ማድረግ ይገባል ሲሉ ም/ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል፡፡
 
በመርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴታ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አልማሀዲን እንደገለፁት ሴቶች የማህበረሰብ ጉልበት መሆናቸዉን ገልፀወዉ ሴቶችን ማክበር፣ መደገፍ እና እኩል ዕድል መስጠት የሁሉም ሀላፊነት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
 
ሴቶች በኢትዮትዮጵያ የህግ የበላይነት እንዲሰፍን እና የተረጋጋ የልማት ስራዎችን እንድታከናዉን በማድረግ እንዲሁም በፖለቲካና በኢኮኖሚዉ መስክ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰዉ ሴቶችን ማክበር ማህበረሰብን ማክበር በመሆኑ ሁላችንም መደገፍ እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ ነፊሳ አሳስበዋል፡፡
 
የቤ/ጉ/ክ/መ/ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ በበኩላቸው ሴት ምሁራን በፖሊሲ ቀረፃና አስተዳደር፣ በማህበራዊ ዕድገትና ሰላም ግንባታ፣ በትምህርት እና በምርምር ሚናቸዉ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በቀጣይም ሴቶች በሀገር ግንባታ ዉስጥ የሚኖራቸዉን ሚና በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት በማማከርና በመደገፍ የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባም ክብርት ወ/ሮ አለምነሻ ገልፀዋል፡፡
 
በበዓሉ ከፌዴራል የመጡ የክብር እንግዶች፣ የክልል አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች፣ ሴት መምህራንና ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡
 
በመርሀ ግብሩ ቀኑን አስመልክቶ የተለያዩ የመወያያ ሰነዶች ፣ቲያትሮችና ሙዚቃዎችም ቀርበዋል፡፡
 
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም በቀረቡ ሰነዶች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ዉይይት አድርገዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *