የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በአሶሳ ከተማ ከሚገኙ የገመሐሩ እና አሶሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዉጤት በሚሻሻልበት ጉዳይ ዙሪያ ዉይይት አድርጓል።
ዩኒቨርሲቲዉ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ ጋር አብሮ እየሠራ መሆኑን በዉይይት መድረኩ ላይ የጠቆሙት የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬከተር ዶ/ር ተፈራ ተሾመ በዚህ በ2018 ዓ.ም ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ለማድረግ ፕሮጀክት ቀርፆ ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀዋል።
በፕሮጀክቱ ገመሐሩ እና አሶሳ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የገለፁት ዶ/ር ተፈራ የዉይይቱ ዓላማም ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በሚሰጥበት ዙሪያ እንደሆነ ተናግረዋል።
በዉይይቱ አገልግሎቱን የሚሰጡ የዩኒቨርሲቲዉ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን እንደ ሀገር በተማሪዎች ዉጤት ላይ የሚታየዉ ዉድቀት ለማከም ከሥር መሠረቱ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን በመድረኩ ተገልጿል።
መምህራንም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ በቁጭት መሥራት እንዳለባቸዉ ተጠቁሟል።
ዩኒቨርሲቲዉ ከትምህርት ቤቶቹ መምህራን ጋር በመቀናጀት ባለችዉ ቀሪ ጊዜ ተማሪዎቹን በመደገፍ የተሻለ ዉጤት እንዲመዘገብ ጥረት ያደርጋሉ ተብሏል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et



