Assosa University

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ ለውስጥ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ለማስጀመር ውል ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲው የውስጥ ለዉስጥ የመንገድ ግንባታ ስራ ለማስጀመር ከአሸናፊዉ ድርጅት ጋር ዛሬ ዉል ተፈርርሟል፡፡
የተፈረመው ውል ከ6 ኪሎ ሜትር በላይ የሆነ የውስጥ ለውስጥ መንገድ አስፋልት ግንባታ ስራን ያካትታል።
 
ተቋራጩ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመንገድ ግንባታዉን አጠናቅቆ ለማስረከብ ዉል የገባ ሲሆን ሲጠናቀቅ ለተማሪዎች ፣ መምህራን እና ለሰራተኞች እንዲሁም ለአካባቢዉ ማህበረሰብ ምቹ የትምህርት አካባቢ ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡
 
በተያዘዉ የበጀት ዓመት ዩኒቨርሲቲው 4.4 ኪሎ ሜትር አጥር ግንባታ የሚሸፍን ስራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን የዩኒቨርሲቲውን ደህንነትና አስተዳደር አቅም የሚጠናክር እንደሆነ ተጠቅሷል።
 
ዉል ስምምነቱም በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም እና በክሮስላንድ ኮንስትራክሽን ማኔጂንግ ዳይሬክተር በአቶ ወልዴ ዘሪሁን ተካሂዷል፡፡
 
ስራው የሁሉምን ባለ ድርሻ አካላት ትብብር የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም ድርሻውን እንዲወጣ ተጠይቋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *