Assosa University

‎የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
‎ቦርዱ ከተወያየባቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች መካከል የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ሲሆን ስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በመማር ማስተማር፣ በምርመር እና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ በአስተዳደር እና መሠረተ ልማት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች አበረታች ዉጤት መመዝገቡን ገምግሟል፡፡
‎በቀጣይም በትምህርት ሚኒስቴር የተጀመሩ ሪፎርም ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ፣ ዩኒቨርሲቲዉ የራሱ የሆነ የተጠናከረ ገቢ እንዲኖረዉ ማድረግ፣ የሚሰሩ ምርመሮች የማህበረሰቡን ችግር ፈችና ተግባር መሆን እንዳለባቸዉ ፣የሚሰጡ አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ እንዲሆኑ ማድረግ እና ሌሎች በስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም የታዩ ዉስንነቶች በቀጣይ ስድስት ወራት የዕቅድ አካል በማድረግ ዉጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ እና የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ የሥራ መመሪያ ሰጥቷል።
‎ቦርዱ በሁለተኛ ደረጃ የተመለከተዉ የተሻሻለዉ አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አዋጅ 1152/2012 ዓ/ም አንቀፅ 57 ንዑስ 1 ላይ በተቀመጠዉ መሰረት የዩኒቨርሲቲዉን ካዉንሰል አባላት መቃኘት በማስፈለጉ በዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ሰብሳቢነት የሚመራ ሆኖ ም/ፕሬዝዳንቶች ፣ ኮሌጂ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች፣ ሥራ አስፈፃሚች፣ የትም/ት ክፍል ሃላፊዎች ፣ቁልፍ አገልግሎት ስጭ ስራ ክፍል ሀላፊዎች እና የተማሪ ተወካዮች(አንድ ሴት እና አንድ ወንድ) የዩኒቨርሲቲዉ ካዉንስል አባል ሁነዉ እንዲካተቱ ይሁንታ ሰጥቷል፡፡
‎ቦርዱ በተመሳሳይ በታላቁ የህዳሴ ግድብ የምርምር ማዕከል በማቋቋም አጀንዳ ላይ በመወያየት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአካባቢዉ ፀጋ በመሆኑ በዚያ ላይ ያተኮረ የምምር ማዕከል እንዲቋቋም ዉሳኔ አሳልፏል፡፡
‎ከዚሁ ጋር ተያይዞም የሚቋቋመዉ የምርምር ማዕከል አስፈላጊ የሆኑ ሂደቶችን ተከትሎ እና የሚያስፈልጉ የመዋቅር አደረጃጀቶች ሲቪል ሰርቪስን በማስፈቀድ ወደ ስራ እንዲገባ በመወሰን እና ሌሎች ወቅታዊ አጀንዳዎችን ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *