Assosa University

‎የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለካዉንስሉ ቀርቦ ዉይይት ተካሂዶበታል

ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
‎በሩብ አመቱ ሪፖርት በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማህበረሰብ ጉድኝት የተሠሩ ሥራዎች አፈጻጸማቸዉ በተቀመጠላቸዉ መለኪያ መሠረት ለካዉንስሉ ቀርበዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።
‎ በሪፖርቱም በርካታ የሪፎርም ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን ሠላማዊ የመማር ማስተማሩ፣ የተቀናጀ የፋይናንስ ማኔጅመንት መረጃ ሲስተም ( IFMIS) ፣የተልዕኮ ልየታን መሠረት ያደረጉ እና ወረቀት አልባ የሆኑ አሠራሮች መተግበራቸዉ በሩብ አመቱ ጥሩ አፈጻጸም ከተመዘገባበቸዉ ሥራዎች በዋናነት ከሚጠቀሱት መካከል ናቸዉ።
‎በሪፖርት ግምገማ ዉይይቱ ላይ ተሠርተዉ ያልተካተቱ እና አንዳንድ አፈጻጸሙን ሊያሻሽሉ ይችላሉ ተብለዉ የታሰቡ አስተያየቶች በካዉንስል አባላቱ ተነስተዉ የየዘርፍ ሀላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዉባቸዋል።
‎የግምገማ ዉይይቱን የመሩት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም በሩብ አመቱ ከበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተስፋ ሰጭ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸዉን ገልጸዉ ሥራዎቻችንን ማቀድ ባህል ማድረግ እንዳለብን አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።
‎በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ በሁለተኛ ሩብ አመትየተሻለ አፈጻጸም መመዝገብ እንዳለበት አሳስበዉ ዩኒቨርሲቲዉ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሞ የተቀበላቸዉን 99 የቁልፍ ተግባራት አመላካች ነጥቦች(KpI)ከምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ጋር ተፈራርመዉ አዉርደዋል።
በተመሳሳይም ም/ፕሬዚዳንቶችም በስራቸዉ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች እና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በመፈራረም የሚያወርዱ ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *