ታህሳስ 01/2017 ዓ/ም
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለንብረት አስተዳደር እና ለሚመለከታቸዉ የስራ ክፍል ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በመንግስት የንብረት አስተዳደር ህጎች እና አተገባበር ዙሪያ ለአራት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነዉ፡፡
በህግ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ በተዘጋጀዉ ስልጠና ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጌታቸዉ ዓለሙ ሲሆኑ ስልጠናዉ በዩኒቨርሲቲዉ የመንግስት ንብረት አስተዳደር፣ አያያዝና አጠቃቀም ህጎች ላይ የፈፃሚ አካላትን ግንዛቤ በማሳደግ ጠንካራ የንብረት ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አክለዉም ሳይንሱን እና ህጉን በማጣጣም የተቋሙን ንብረት በባለቤትነት ስሜት መያዝና ማስተዳደር እንደሚገባ ገልፀዉ ስልጣኞች ስልጠናዉን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡
በመጀመሪያ ቀን ዉሎ በመንግስት አስተዳደር፣ ህግና አተገባበር ጉዳዮች ላይ በመምህር ዘሪሁን ይታየዉ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በቀጣይ ቀናትም በስቶክ አስተዳደር የህግ ማዕቀፍ ላይ ስልጠናዉ እንደሚቀጥል ተገልጧል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#