ህዳር 26/2017 ዓ/ም
የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸዉ የስራ ሃላፊዎች በዩኒቨርሲቲዉ እየተከናወኑ በሚገኙ የግንባታና መሰረተ ልማት፣ የምርምርና ማህብረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት አፈፃፀም ላይ የመሥክ ምልከታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
የፕሮጀክት አስተዳደር አጋርነትና ሀብት ማፈላለግ ቡድን መሪ አቶ ገመቹ እምሩ የመስክ ምልከታዉን ዓላማ በተመለከተ ባደረጉት ገለፃ በዩኒቨርሲቲው እየተተገበሩ የሚገኙ የግንባታና መሰረተ ልማት እንዲሁም የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ላይ መልካም ተሞክሮዎችና እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በመለየት የተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠልና የሚያጋጥሙ ክፍተቶች ላይ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር የሆኑት ተፈራ ተሾመ (ዶ/ር) በዩኒቨርሲቲዉ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የአካባቢዉን ማህበረሰብ ችግር የሚፈቱና በሀገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ እየተከናወኑ የሚገኙ የግንባታ ፕሮጀክቶች እና የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ማዕከል እንዲሁም በኡራ፣ አብርሃሞ እና በባምባሲ ወረዳዎች የለሙ የጤፍ እና የማሽላ ዘር ብዜት፣ በአሶሳ እና በባምባሲ ከተማዎች የሚገኙ የነፃ የህግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የመስክ ምልከታ ተደርጎባቸዋል። በቀጣይም በሌሎች የምርምር ማዕከላት የመስክ ምልክታው እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#