Assosa University

ዩኒቨርሲቲዉ የዘር ብዜት ሥራዉን አጠናክሮ ቀጥሏል

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንድሁም በቴክኖሎጂ ሽግግሩ በርካታ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ያለ ተቋም ነዉ።
ዩኒቨርሲቲዉ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በማኦ ኮሞ ወረዳና በአሶሳ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች በተመረጡ አርሶ አደሮች ማሳ ላይ ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂን ተግባር ላይ በመዋል የስንዴ፣የማሽላ፣የጤፍ እና የአኩሪ አተር አዝርኢቶች የዘር ብዜት ሥራ ሲያካሂድ ቆይቷል።
በዚህ በ2017 ዓ.ም የምርት ዘመንም በግብርና ኮሌጅ ተመራማሪዎች ሙያዊ አጋዥነት በኡራ ወረዳ በመንደር 20 ቀበሌ በተመረጡ 25 አርሶ አደሮች በ 15 ሄክታር መሬት ላይ የጤፍ ዘር ብዜት ስራ ተሠርቷል።
በተመሳሳይም በአብረአሞ ወረዳ በአምባ 12 ቀበሌ በ 8 አርሶ አደሮች በ15 ሄክታ ማሳ ላይ የጤፍ ዘር ብዜት ሥራ ተከናዉኗል።
ተመራማሪዎቹም ከማሳ ዝግጅት አስከ አዝመራ ከተታ ሳይንሱን መሠረት ያደረገ ስልጠና በመስጠት ሙያዊ እገዛ እና ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸዉ አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።
የኡራ እና አብረአሞ ወረዳ አርሶ አደሮች ዩኒቨርሲቲዉ ላደረገላቸዉ የምርጥ ዘር እና የሙያ ድጋፍ በእጅጉ አመስግነዉ ምርጥ ዘሩንም በማባዛት ለሌሎች አርሶ አደሮች ተደራሽ እንድሆን በማድረግ የክልሉን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በሚሠራዉ ሥራ የድርሻቸዉን እንደሚወጡ ገልጸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *