ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እየተከናወኑ ያሉ የግንባታ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን የግንባታ አማካሪ መሃንድሶች፣የግንባታ ተቋራጭ ድርጅቶች በተገኙበት የግንባታ የአፈጻጸም ሂደታቸዉ ተገምግሟል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ከማል አብዱራሂም(ዶ/ር) እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዚዳንት ጌታቸዉ አለሙ (ዶ/ር) በመሩት ዉይይት ተቋራጭ ድርጅቶቹ የዕቃዎች የዋጋ ግሽበትን ተከትሎ የገንዘብ እጥረት ያጋጠማቸዉ በመሆኑ ግንባታዎችን በተያዘላቸዉ ጊዜ ለመጨረስ እንደተቸገሩ ገልፀዉ ከአማካሪዎች እና ከዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ጋር በመወየየት በሚሠጣቸዉ አቅጣጫ መሠረት ስራቸዉን እያከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት እየተከናወኑ ያሉ የግንባታ ፕሮጀክቶች የድርጊት መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ የፕሮጀክት ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና አማካሪዎች ጥራታቸዉን ጠብቀዉ መሰራታቸዉን ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ማድርግ እንደሚያስልግ አስገንዝበዋል፡፡ ለግንባታ ተቋረጮችም ሁሉም የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በትኩረት ተሰርተዉ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ አንጠዲጠናቀቁ አጽንኦት ሰጥተዉ አሳስበዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#D