የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዲሱን ተቋማዊ መዋቅር በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን በመዋቅሩ መሰረት ቡድን መሪና ከዚያ በላይ መደቦች ላይ ከተመደቡ አመራሮች ጋር ስለተቋሙ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ በዛሬው እለት ውይይት አካሄዷል።
በዉይይቱ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ስለ አዲሱ ተቋማዊ አደረጃጀት እና ዓላማው ማብራሪያ ሰጠዋል።
በአዲሱ መዋቅር የዩኒቨርሲቲው የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ኃላፊ ሆነው የተመደቡት አቶ አዲሱ አዳሜ የዩኒቨርስቲውን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስመልከት ሰነድ አቅርበዋል።
በውይይቱ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንቶች የተሳተፉ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕረዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው አለሙ ውይይቱን በጋራ መርተውታል።
(ታህሳስ 02/2016 ዓ.ም)
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት/ Assosa University Public and International Relations Directorate
Face book: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficial
Telegram: https://t.me/assosauniversity_official
Website: https://www.asu.edu.et
Email: pir@asu.edu.et
PoBox 18