Assosa University

ማስታወቂያ

ለሁሉም የአሶሳ ዩኒቨረሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ

የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ሰዓት የአለም ስጋት መሆኑ በብዙሀን መገናኛዎች እየተሰራጨ ይገኛል፡፡ የኮሮና ቫይረስ መሰራጫ መንገድ በሰዎች ንክክ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲ ሰዎች በብዛት የሚገኙበት ቦታ በመሆኑ  የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የበሽታዉ ሁኔታ እስክረጋጋ ድረስ በዩኒቨርሲቲዉ ሊወሰዱ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ በመወያየት የሚከተሉትን ወሳኔዎች አስተላልፏል፡-

  • 7 አባላት ያሉት ግብረ ኃይል አቋቁሞ የበሽታዉን ሁኔታ በየቀኑ እየተከታተለ እና መረጃ እያደራጀ  የተቋሙን ሁኔታ ለህዝብ ተደራሽ ያደረጋል
  • ከ08-07-2012 ዓ/ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ት/ት እንዳይናር ተደረጓል
  • ከ08-07-2012 ዓ/ም ጀምሮ መምህራን ለተማሪዎች ፊት ለፊት የሚያሰተምሯቸዉን ት/ቶች በማሰቀረት ለተማሪዎች Hand out, reference books,online and soft copy materials በበቂ ደረጃ በማቅረብ እና ሌሎች ዘዴዎችን በመጠቀም የበግላቸዉ/ በክፍላቸዉ ሆነዉ እንዲያነቡ፤ መምህራን በኢሜይልና በተለያዩ ዘዴዎች የመማር ማስተማሩን ስራ አንዲመሩት የተወሰነ ሲሆን፤ ይህንን ተግባራዊ ማድረጋቸዉን አንዲረጋገጥ
  • ተማሪዎች በምግቤትና ላይበራሪ አካባቢ መተፈፈግን ለማስቀረት የመቀመጫዎች ጥግግት እንዳይኖር የአገልግሎት ሰዓት ማራዘም
  • አስገዳጅ ስብሰባዎች እንኳ ቢኖሩ ሰፋ ባለአዳራሽ አንዲካሄዱ
  • የተለየ የበሽታዉ ምልክት ቢከሰት የተጠርጣሪዉ ማቆያ ተለይቷል

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *