Assosa University

3ኛዉ የተግባር ተኮር( Applied science Universities) የጋራ ፎረም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነዉ

በሀገር ደረጃ 15 ዩኒቨርሲቲዎች የተግባር ተኮር ሆነዉ ተለይተዉ የጋራ ፎረም በመመስረት ከዚህ በፊት ሁለት የጋራ ፎረሞችን ያካሄዱ ሲሆን የዘንድሮዉን ሦስተኛዉን የጋራ ፎረም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ይገኛል።
 
‎በጋራ ፎረሙም የአስራ አምስቱ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች ፣ም/ፕሬዚዳንቶች ፣ ትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር እና ዞን አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የጋራ ፎረሙ እየተካሄደ ነዉ።
‎የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ለተሳታፊዎቹ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸዉ ዩኒቨርሲቲዉ ባለፉት 14 ዓመታት በርካታ ዉጤታማ ሥራዎች ያከናወነ መሆኑን ጠቁመዉ የክልሉ መንግስት እና የከተማ አስተዳደሩ በሚያደርግልን ያልተቋረጠ እና ጠንካራ ድጋፍ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ስራ በማካሄድ ላይ እንገኛለን ብለዋል።
 
‎ በጋራ ፎረሙም የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተሞክሮ እና ልምድ ቀርቦ የጋራ ዉይይት የሚደረግበት ሲሆን የጋራ ፎረሙ አባላት የአሶሳ ፣ የዲሬዳዋ ፣የአምቦ ፣የወሎ ፣ የአርሲ፣የኮተቤ፣የወላይታሶዶ፣የደብረብርሃን፣የወልቂጤ፣የሠመራ፣ የዲላ፣የጂግጂጋ፣የደብረ ማሪቆስ፣የአክሱም እና የወለጋ ዩኒቨርሲዎች ፕሬዚዳንቶች እና ም/ፕሬዚዳንቶች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።
 
‎የዚህ ዓመት መሪ ቃልም ” Birdging theory and practice through UAS for Sustainable a context responsive future”የሚል ነዉ።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *