የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቴክኒክና ሙያ እና የሥራ እድል ፈጠራ ኤጀንሲ ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ፊርማ አካሂደዋል። የስምምነቱም አላማ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ፣ ችግር ፈች የጥናትና የማማከር አገልግሎት ለመስጠት እና የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠናዎችን በመስጠት የሰው ሃይል ልማትን ውጤታማ ለማድረግ እንድሁም የተማሪዎችን የመማር ማስተማር ክህሎት የሚደግፉ የተግባር ልምምድ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ የጋራ የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ፊርማ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ከማል አብዱረሂም ገልፀዋል ።