ዩኒቨርሲቲዉ የቤተሰብ ምክር አገልግሎት ከሚሰጥ ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት ተፈራረመ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የቤተሰብ ምክር አገልግሎት ከሚሰጥ Family Guidance Association of Ethiopia ከተባለ ድርጅት ጋር ለተማሪዎች በስነ ተዋልዶ እና በአባለ ዘር በሽታዎች ዙሪያ የግናዛቤ መፍጠር ፣የመቆጣጠርና የመከላከል ስራዎችን ለመስራት ዛሬ ተፈራርሟል፡፡ድርጅቱ በቀጣይ ሶስት አመታት ለተማሪዎች በስነ -ተዋልዶ ጤና ፣በአላስፈላጊ እርግዝና መከላከል እንዲሁም በኤች.አይ.ቪ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ለመስራት የድርጅቱ የኤች.አይ.ቪ መቆጣጠርና መከላከል አስተባባሪ አቶ ጉድሳ እምሩ ከዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም ጋር ተፈራርመዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉንTwitter:Assosa University (@AssosaU) / XWhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21PFacebook: https://www.facebook.com/AssosaUniversityOfficialTelegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2NkEmail: pir@asu.edu.etInstagram: https://www.instagram.com/asueduet/#