Assosa University

ዩኒቨርሲቲዉ ከክልሉ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል የጋራ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ

ዩኒቨርሲቲዉ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ስራ እና ክህሎት ቢሮ በጋራ ለመስራት በዛሬዉ ዕለት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
‎በፊርማ ስነ ሥርዓቱ ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም የስምምነት ሰነድ መፈራረሙን ዓላማ ሲገልጹ ወጣቱ ከአልባሌ ቦታ እንዳይዉል ለመታደግ በሥራ ፈጠራ እና ክህሎት ልማት ላይ በጋራ ለመስራት ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል።
‎በተመሳሳይም የዩኒቨርሲቲዉ የምርምር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብደልሙህስን ሀሰን የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተግባር ሳይንስ ሆኖ በመለየቱ የኢንዱስትሪዉን ችግር መፍታት የሚችሉ ተማሪዎችን ማሠልጠን እና ማስመረቅ ላይ የሚያተኩር በመሆኑ በጋራ ከክልሉ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ጋር ለመስራት ስምምነት መደረጉ ሥራዎቻችንን እዉን ለማድረግ የሚያስችል ይሆናል ብለዋል።
‎የክልሉ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሰላም ሸንገል በበኩላቸዉ የተሠጠንን ሀገራዊ የሪፎርም ሥራዎች ለመተግበር እና የላቀ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ከዩኒቨርሲቲዉ ጋር በትብብር መስራት መቻላችን ቢሮዉን ዉጤታማ ለማድረግ ያስችለናል ብለዋል።
‎በስምምነት ሰነዱ ላይ የስራ ፈጠረ እና ከህሎት ልማት ስልጠናዎችን ለወጣቶች መስጠት ፣ የጥናትእና ምርምር ሥራዎችን መስራት እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ለተግባር ትምህርት መሠልጠኛነት በጋራ ለመጠቀም ከተጠቀሱት ነጥቦች መካከል ናቸዉ።
‎ በጋራ ስምምነት ሰነዱ ላይም የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም እና የክልሉ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልሰላም ሸንገል ፈርመዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *