በግማሽ አመቱ ሪፖርት በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአስተዳደር እንዲሁም በማህበረሰብ ጉድኝት የተሠሩ ሥራዎች ለእያንዳንዳቸዉ ግቦች በተቀመጠላቸዉ ዕቅድ መሠረት አፈጻጸማቸዉ ቀርቦ ካዉንስሉ ዉይይት አድርጎባቸዋል።
በግማሽ አመቱ ሪፖርትም ሠላማዊ የመማር ማስተማሩ ሥራ በተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ መሄዱ ፣ ከእቅድ አኳያ በጀትን መጠቀም መቻሉ፣በማህበራዊ ሀላፊነትና ማህበረሰብ ተሳትፎ ዉጤታማ ሥራዎች መሠራታቸዉ፣ ለሰራተኞች እና ለመካከለኛ አመራሩ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱ ጥሩ አፈጻጸም ከተመዘገባበቸዉ ተግባራት መካከል ለምሳሌነት ተጠቅሰዋል።
በሪፖርት ግምገማ ዉይይቱ ላይ የየስራ ክፍል ሀላፊዎች እና የዘርፍ ሀላፊዎች ተሠርተዉ ያልተካተቱ እና አንዳንድ አፈጻጸማቸዉ መስተካከል ቢኖርባቸዉ ያሉኣቸዉን ሀሳብ እና አስተያየት አንስተዉ ማሻሻያ እንድደረግባቸዉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የግምገማ ዉይይቱን የመሩት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም በግማሽ አመቱ ሪፖርት ግምገማ የካዉንስል አባላቱ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል በባለቤትነት ስሜት ሀሳብ እና አስተያየት መስጠት ተቋሙን ለመቀየር ከልብ ከመፈለግ የሚመነጭ የባለቤትነት ስሜት ነዉ ሲሉ ገልጸዋል።
በተጨማሪም በአቀድነዉ ዕቅድ ልክ ዉጤት ማስመዝገብ ከሁሉም አመራር እና ሠራተኛ እንደሚጠበቅ አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በሁለተኛዉ ግማሽ አመት
የተሻለ አፈጻጸም መመዝገብ እንዳለበት እና ጥብቅ የስራ ስምሪት በማድረግ እንድሁም ሁሉም ሥራ ክፍሎች ተግባብተዉ እና ተናበዉ ለጋራ ተቋማዊ ተልዕኮ መስራት እንደሚገባ አሳስበዉ የሪፖርት ግምገማዉ ተጠናቋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#




