ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
በሩብ አመቱ ሪፖርት በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማህበረሰብ ጉድኝት የተሠሩ ሥራዎች አፈጻጸማቸዉ በተቀመጠላቸዉ መለኪያ መሠረት ለካዉንስሉ ቀርበዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል።
በሪፖርቱም በርካታ የሪፎርም ሥራዎች የተካተቱ ሲሆን ሠላማዊ የመማር ማስተማሩ፣ የተቀናጀ የፋይናንስ ማኔጅመንት መረጃ ሲስተም ( IFMIS) ፣የተልዕኮ ልየታን መሠረት ያደረጉ እና ወረቀት አልባ የሆኑ አሠራሮች መተግበራቸዉ በሩብ አመቱ ጥሩ አፈጻጸም ከተመዘገባበቸዉ ሥራዎች በዋናነት ከሚጠቀሱት መካከል ናቸዉ።
በሪፖርት ግምገማ ዉይይቱ ላይ ተሠርተዉ ያልተካተቱ እና አንዳንድ አፈጻጸሙን ሊያሻሽሉ ይችላሉ ተብለዉ የታሰቡ አስተያየቶች በካዉንስል አባላቱ ተነስተዉ የየዘርፍ ሀላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዉባቸዋል።
የግምገማ ዉይይቱን የመሩት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ከማል አብዱራሂም በሩብ አመቱ ከበርካታ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተስፋ ሰጭ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸዉን ገልጸዉ ሥራዎቻችንን ማቀድ ባህል ማድረግ እንዳለብን አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ በሁለተኛ ሩብ አመትየተሻለ አፈጻጸም መመዝገብ እንዳለበት አሳስበዉ ዩኒቨርሲቲዉ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሞ የተቀበላቸዉን 99 የቁልፍ ተግባራት አመላካች ነጥቦች(KpI)ከምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ጋር ተፈራርመዉ አዉርደዋል።
በተመሳሳይም ም/ፕሬዚዳንቶችም በስራቸዉ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች እና ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር በመፈራረም የሚያወርዱ ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#









