ለአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከህዳር 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ በአሶሳ ከተማ ብሌንዳና ሆቴል ሲሰጥ የነበረው የፕሮጀክቶች አዘገጃጀት፣አስተዳደር እና አተገባበር እንድሁም የግንኙነት አውታር ሥልጠና ዛሬ ተጠናቋል። በሥልጠናው ላይም Grant Development & Management, እና Networking and partnership strategyበሚል ርዕስ ላይ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹም ቡድን በመከፋፈል በጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በሥልጠናው ማጠናቀቂያም በባምባሲ ከተማ የሚገኘው የዩኒቨርሲቲው የሥልጠና፣ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ተጎብኝቶል።ማዕከሉ ለተማሪዎች የተግባር ትምህርት መማሪያ፣ለምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት መስጫ ነት የሚውል ማዕከል መሆኑን የዩኒቨርሲቲው የምር/ማህ/አገ/ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሀይማኖት ዲሳሳ ገልፀዋል። በማዕከሉ የሚገኘው የንብ እርባታ -የምርምር ማዕከልና ውጤቱ ምልከታ ተካሂዶባቸዋል። በስልጠናው ማጠናቀቂያ ወቅት የተገኙት የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ረ/ፕሮፌሰር አበራ በይሳ በቀጣይ የአከባቢውን ማህበረሰብ ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመስራት ስልጠናው ግብዓት እንደሚሆን ገልጸዋል። በመጨረሻም ለስልጠናው ተሳታፊዎች በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በሆኑት በረ/ፕሮፌሰር አበራ በይሳ እና በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ ዕጩ ዶ/ር አብዱልሙህስን ሀሰን ሰርትፍኬት ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።