በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በፕሬዝዳት ጽ/ቤት ዘርፍ ስር የሚገኙ ስራ አስፈፃሚዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት በ2017በጀት ዓመት በዘርፉ በስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የስድስት ወራት የዘርፉ ሥራ ክፍሎች ዕቅድ ክንዉን አፈፃፀም በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በመ/ር ንጋቱ አምቢሳ የቀረበ ሲሆንበዘርፉ ሀላፊ በዶ/ር ከማል አብዱራሂም መሪነት በተካሄደ ዉይይት ሪፖርቱ በጥልቅ ተገምግሟል።
ፕሬዝዳንቱም በሪፖርት ግምገማዉ ላይ ሌሎችን የመማር ማስተማር፣የምርምር እና የአስተዳደር ዘርፎችን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ዘርፍ ከተሰጠን ተግባርና ሀላፊነት አንፃር ስራዎችን በሙሉ አቅም መስራት እንደሚጠበቅብን ማሰብ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም በዘርፉ የግማሽ በጀት አመት የስራ አፈፃፀም የተገኙ ጠንካራ ጎኖች ጎልብተው የሚቀጥሉበትን እንዲሁም የታዩ ክፍተቶች የሚስተካከሉበትን አቅጣጫ ፕሬዝዳንቱ አመላክተዋል።
በቀጣይ ቀናትም ሁሉም ዘርፎች በዘርፋቸዉ ሪፖርታቸዉን ገምግመዉ ካጠናቀቁ በኋላ የተቋሙ ሪፖርት ለዩኒቨርሲቲዉ ካዉንስል ቀርቦ ዉይይት ይካሄድበታል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
WhatsApp group: https://whatsapp.com/channel/0029Vau844l9xVJkZ3GXR21P
Telegram: https://t.me/+J9ZDxvCigO0yN2Nk
Email: pir@asu.edu.et
Instagram: https://www.instagram.com/asueduet/#