Assosa University

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ዛሬ ባካሄደዉ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል፡፡
‎ሴኔቱ በአንደኛ አጀንዳዉ የዩኒቨርሲቲው የ2018 ዓ/ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ ለነበሩ የመደበኛ፣ የሳምት መጨረሻ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎችን ዉጤት እንዲሁም የመጀመሪያ ዓመት የተማሪዎች የዲፓርትመት ምደባ በሬጅስተራር ጽ/ቤት ሃላፊ በዶ/ር ሀብታሙ ሸንቁጥ አቅራቢነት በመገምገም ስታተሱን አፅድቋል፡፡
‎ሴኔቱ በመቀጠል የተመለከተዉ የዩኒቨርሲቲዉን የሰኔት መተዳደሪያ ደንብ (Senate Legislation) ክለሳ በአዲሱ የትምህርት ሚኒስቴር የሪፎርም ስራዎች መሠረት በመቃኘት የተደረጉ ማስተካከያዎችን ተወያቶ አፅድቋል፡፡
‎በሦስተኛ ደረጃ ሴኔቱ የተመለከተዉ አጀንዳ የከፍተኛ ትምህርት የኦን ላይን ትምህርት
‎( Electronic Learing) የአፈፃፀም መመሪያን ደንብ ቁጥር 1044/2025 ተወያይቶ አፅድቋል።
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን
Twitter:Assosa University (@AssosaU) / X
Email: pir@asu.edu.et

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *